ርዕስ:የንግድ ስም ምዝግባ

የአገልግሎቱ አጭር መግለጫ
በሚኒስቴር መስራቤቱ የዋና ምዝገባ ያካሄዱና በዚሁ መሰረት የንግድ ስራ ፈቃድ የተሰጣቸው

ነጋዴዎች የንግድ መደብሮቻቸውን የሚሰይሙአቸው የንግድ ስሞች ስለመመዝገቡ የሚሰጥ የባለቤትነት
ማስረጃ ነው።
የንግድ ስም አንድን የንግድ ተቋም ከሌላው ለመለየት የሚያገለግል መለያ ነው፡፡

የንግድ ስም የንግድ ስራ ስም እና የባለቤት ስም በመባል በሁለት ይከፈላል፡፡
የንግድ ስራ ስም ፦
ማለት አንድ የንግድ ተቋም የሚለይበት ዘዴ በህጋዊነት የሚንቀሳቀስበት አግባብ ማለት ሲሆን የንግድ ስራ ስምን ለመጠቀም

በህግ ከተደነገገ አካል ስሙን በማስመዝገብ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
የባለቤት ስም ፦
ማለት በዜግነት መታወቂያ ወረቀቱ ላይ የተቀመጠውን ስም በመጠቀም ቀጥታ የንግድ ስራው መጠሪያ በማድረግ ማስመዝገብና

መንቀሳቀስ ማለት ነው፡፡ አንድ ግለሰብ በንግድ ስም መዝገብ መመዝገብ ሳያስፈልገው በራሱ ስም በቀጥታ የንግድ ምዝገባ በማድረግ

ወደ ንግድ ስራ እንቅስቃሴ መግባት የሚችል ሲሆን የንግድ ስራ ስም ለማስመዝገብና ለመንቀሳቀስ ግን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን

መስፈርቶች በማሟላት መመዝገብ ይኖርበታል፡፡
አጠቃላይ የአገልግሎቱ የአሰራር መመሪያ(18 መመሪያዎች)

የሚጠየቁ መስፈርቶች
1) የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ስያሜ እዲሰጠው/እንዲሰጣቸው የቀረቡ
የንግድ ስራ ፍቃድ/ፍቃዶች ፎቶ ኮፒ

2) አመልካቹ የራሱንየቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ከፎቶ ኮፒጋር፤
በተጨማሪም ጉዳዩን የሚያስፈፅመው ሰው
ወይንም አመልካቹ ስራ አስኪያጅ ካልሆነ በውልና ማስረጃ
የፀደቀ የውክልና ደብዳቤ

3)ስድስት ወር ያልሞላው ሁለት የስራ እስኪያጁጉርድ ፎቶግራፍ፤

4)የንግድ ስሙ እንዲጣራ የሚሞላውን ፎርም መሙላት
ዝርዝር የአገልግሎቱ ሂደት

1)የቀረበው የንግድ ስም ከላይ በቀረቡት መስፈርቶች መሰረት መሆኑን ማረጋገጥ

2)የቀረቡት የንግድ ስራ ስም ጥያቄዎች በመረጃ ቋት ውስጥ በሌላ ያልተያዙ መሆኑን ማረጋገጥ

3)የተያዙ ከሆነ ሌላ አማራጭ የንግድ ስራ ስም እንዲያቀርቡ ማድረግ

4)የግለሰብ ስም ከሆነ እስከ ቅድም አያት ድረስ በመመዝገብ የተለየ መሆኑን ማረጋገጥ

5)ስሙ በጋዜጣ እንዲወጣ ለ ፕሬስ ድርጅት ደብዳቤ መፃፍና መላክ(የሚገኝበት ቦታ)

6)ከ 15 ቀን በኋላ በቀረበው የንግድ ስም ላይ ተቃዋሚ ካልቀረበ የጋዜጣውን ሁለት ቅጂ በመያዝ
የምስክር ወረቀት አትሞና ፈርሞ መስጠት

7)በዚሁ መሰረት የንግድ ስራ ስም ምዝገባውን በማጽደቅ ከንግድ ስራ ምዝገባ ጋር በአንድነት ማከናወን