ርዕስ:የተቋማት ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠት

የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስታንዳርዳይዜሽንና ሬጉሌሽን ዳይሬክቶሬት በመገናኛና በመረጃ ቴክኖሎጂ መስክ ለተሰማሩ ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡ እነዚህ ድርጅቶች የስልክ፣ የሞባይል እና መሰል የድምጽና ዳታ መገናኛ መሳሪያዎች ቀፎዎች እና መለዋወጫዎች፣ የቴሌኮሙኒኬሽ ኬብል እና ማዞሪያ መሳሪያዎች፣ መለዋወጫዎችና የመገልገያ እቃዎችን፣ የኮምፒውተር፣ የኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎች፣ መለዋወጫዎችና የመገልገያ መሳሪያዎች የመፈብረክ፣ የጅምላ ንግድ የችርቻሮ፣ የጥገና፣ የአስመጪነት፣ የላኪነት፣ የኔትወርክ ዲዛይን፣ ዝርጋታና ትግበራ፣ የመረጃ ቋት ስራዎች እንዲሁም የማማከር ስራዎች ላይ የተሰማሩ ናቸው፡፡
ይህን አገልግሎት ለማግኘት ድርጅቶች የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላትና የባለሙያዎችና ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በመፈብረክ የስራ ዘርፍ የሚሰማሩ ድርጅቶች የስራ ቦታ ወይም ወርክሾፕና የመገልገያ መሳሪያዎች ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ማመልከት የሚችሉ እነማን ናቸው?
በመገናኛና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የንግድ ተቋማትና ግለሰቦች:: አገልግሎቱ የሚፈጀው ጊዜ፡ አገልግሎቱን ለማግኘት ከአመለከቱ በኋላ በ 30 ደቂቃ ውስጥ ያልቃል፣ በመፈብረክ የሥራ ዘርፍ ላይ ከጠየቁ በስተቀር ቅድመ የቦታ ጉብኝት ስለሚያስፈልግ፤

በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ለሚሰማሩ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ለማግኝት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች፡-