ርዕስ:ለጭነት ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች የድንበር ተሻጋሪ ፈቃድ መስጠት
የጭነት ትራንስፖርት ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች ወደ ጎረቤት ሃገራት ማለትም ጂቡቲና ሱዳን
ለመግባት በቅድሚያ የድንበር ተሻካሪ ፈቃድ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል፤ የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን
የአገልግሎት ጥያቄውን በመገምገምና ለአገልገሎቱ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸውን በማረጋገጥ
ለጭነት ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች የድንበር ተሻጋሪ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ የተሽከርካሪው ባለንብረት
ወይም ህጋዊ ጉዳይ አስፈጻሚ ፈቃዱን መውሰድ የሚችል ሲሆን የድንበር ተሻካሪ ፈቃዱ ለሱዳን ከሆነ
አሽከርካሪው እና ረዳቱ የጣት አሻራ ለመስጠት በአካል መገኘት ይጠበቅባቸዋል፤
ለጭነት ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች የድንበር ተሻጋሪ ፈቃድ አገልግሎት ለማግኘት አመልካቾች የሚከተሉትን አስር መስፈርቶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡
